Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት አምስት ወራት ከማእድን ዘርፍ ከ 302 ሚሊየን ዶላር በላይ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አምስት ወራት ከማእድን ዘርፍ ከ 302 ሚሊየን ዶላር በላይ መገኘቱን የማእድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የማእድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ 4 ሺህ 83 ኪሎ ግራም ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቦ 299 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ገልጸዋል።
ከዚህ ባለፈም ከጌጣጌጥ ማእድናት 3 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ተገኝቷል ነው ያሉት።
ሚኒስቴሩ በማእድን ማምረትና ምርምር ላይ እንዲሰማሩ ፍቃድ ከተሰጣቸው መካከል 63 ተቋማት ባሳዩት ደካማ አፈጻጸም ምክንያት ፈቃዳቸው መሰረዙንም ገልፀዋል።
ከእነዚህም ውስጥ 38ቱ ተቋማት በማእድን ምርት ላይ የተሰማሩ ሲሆን 25ቱ ተቋማት ደግሞ በማእድን ምርምር ላይ የነበሩ ናቸው ተብሏል።
በብስራት መለሰ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.