Fana: At a Speed of Life!

የፀረ ጾታዊ ጥቃት (የነጭ ሪቫን) ቀን በጅግጅጋ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፀረ ጾታዊ ጥቃት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ29ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ በጅግጅጋ ተከበረ፡፡
በበዓሉ የሶማሌ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ፣ የሴቶችና ህፃናት ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂና የኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ አየርላንድ፣ ጃፓን፣ ቱርክና ስዊድን አምባሳደሮች ተገኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅት ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ መንግስት የሴቶችን እኩልነት ለማረጋገጥ ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የሶማሌ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በበኩላቸው÷ በክልሉ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል በክልሉ የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት መሪዎችንና የሚመለከታቸውን የመንግሥት ተቋማት በማቀናጀት ለመከላከል የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
የኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ አየርላንድ፣ የስዊድን፣ ጃፓንና ቱርክ አባሳደሮች ኢትዮጵያ የሴቶችን ጥቃት ለመከላከልና የሴቶችን እኩልነትን ለማረጋገጥ እያደረገች ያለውን ጥረት አድንቀዋል።
በዓሉ “በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የማይታገስ ትውልድ እንፍጠር” በሚል መሪ ቃል መከበሩን የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.