Fana: At a Speed of Life!

በጁንታው ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ዳግም በማያንሰራራ መልኩ ሊጠናቀቅ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፀረ ለውጥ በሆነው የህወሓት ጁንታ ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ዳግም በማያንሰራራ መልኩ ሊጠናቀቅ እንደሚገባ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ገለጹ።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ተወያይቷል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ረዳት ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያዊነት ዋጋ የከፈለ ትልቅ ህዝብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ህዝቡ በአላስፈላጊ ጊዜ አላስፈላጊ ዋጋ የከፈለ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባ ፀጋዬ አሁን ላይ ህዝቡ የለውጡን ፍሬ እየቀመሰ መሆኑን ጠቅሰው በዚህም ክልሉን ለማልማትም በጋራ እንደሚሰሩ አስረድተዋል።
የትግራይ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶክተር ሀድጎ ኪሮስ በበኩላቸው በእነዚህ ጥቂት የህወሓት ቡድን የትግራይ ህዝብም በከፍተኛ ሁኔታ የችግሩ ሰለባ ሆኗል ብለዋል።
የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ አለመሆናቸውን የገለጹት ዶክተር ሀድጎ የትግራይ ህዝብ ጨቋኝን ለመቀየር መታገሉን አንስተዋል፡፡
በመድረኩ የትግራይ ተወላጆች በጽንፈኛው ቡድን የተፈጸመውን አስነዋሪ ተግባር አውግዘው የትግራይ ህዝብ ለረጅም አመታት መጎዳቱን ተናግረዋል።
ተወላጆቹ በሚኖሩበት አካባቢ መብታቸው ተከብሮና ተደስተው እንደሚኖሩ መግለፃቸውን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.