Fana: At a Speed of Life!

ሲቪክ ማህበራት ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና የተመለከተ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተዘጋጀውና ሲቪክ ማህበራት ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና የተመለከተው ውይይት ተካሄደ፡፡

የሰላም ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር አብዲ ዘነበ ሲቪክ ማህበራት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እና የዳበረ ዴሞክራሲ ለመገንባት ትልቅ ሚና አላቸው ብለዋል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጠሪ ተቋማት እና የስትራቴጂክ አጋርነት ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ሻንቆ ደለለኝ በበኩላቸው፥ የሰላም ሚኒስቴር ሲቪክ ማህበራት የውስጥ አሰራራቸውን እንዲያዘምኑ እና የሰላም ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ እገዛ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ሲቪክ ማህበራት ያሉባቸውን ተግዳሮቶች አስመልክቶ የጥናት ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን፥ በመንግስትና በሲቪክ ማህበራት መካከል ጠንካራ መተማመን አለመኖሩ ተነስቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሁሉም ሲቪክ ማህበራት የተስማሙበት ሀገራዊ አጀንዳ አለመቀረፁ እንዲሁም የሲቪክ ማህበራት የራሳቸው የአቅም ውስንነት እና የእርስ በርስ ትብብር ማነስ በችግርነት ተጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ በፌደራል ደረጃ የተመዘገቡ ከ2 ሺህ 500 በላይ የሲቪክ ማህበራት መኖራቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.