Fana: At a Speed of Life!

በሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት አውቶቡስ ማቆሚያ ከፈነዳው ቦንብ በተጨማሪ በባለሙያ ሳይፈነዱ የከሸፉ ቦንቦች መኖራቸወን ፖሊስ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት አውቶቡስ ማቆሚያ ከፈነዳው ቦንብ በተጨማሪ በባለሙያ ሳይፈነዱ የከሸፉ ቦንቦች መኖራቸወን ፖሊስ ገለጸ።
በአዲስ አበባ ሰሚት አካባቢ በሚገኝ በሸገር አውቶቡስ ማቆሚያ የፈነዳ ቦንብን ተከትሎ 11 የሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት ሰራተኞች በተጠረጠሩበት ወንጀል ዛሬ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።
ተጠርጣሪዎቹ በነሀይላይ ተክሉ በሚል መዝገብ የተካተቱት 11 የሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት ሰራተኞች በህዳር 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ በሰሚት አውቶቡስ ማቆሚያ ላይ የፈነዳ ቦንብን ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው።
በዚህ መዝገብ የተካተቱ የጥበቃ ሰራተኞች እና የአውቶቡስ አሽከርከሪና ቴክኒሻኖችም ይገኙበታል።
መርመሪ ፖሊስ ተጠረጣሪዎቹ ላይ ከዚህ በፊት በተሰጠው 11 ቀናት ጊዜ በርካታ የምርመራ ስራ ማከናወኑን ገልጾ÷ የምስክር ቃል መቀበሉን የገለጸው ፖሊስ በእለቱ ቦንቡ ሲፈነዳ የነበረውን የስልክ ልወውጥ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።
ፖሊስ በእለቱ በቦታው በባለሙያዎች ሳይፈነዳ የከሸፈ ቦንቦች መኖራቸውን ጠቁሞ÷በቦታው የተገኘ ካሜራ ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተቋም መላኩን ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ በመታሰራቸው ምክንያት ቤተሰቦቻቸው ለቀለብ እና ለቤት ኪራይ መቸገራውንና በዋስ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
መዝገቡን የተከታተለው ፍርድቤቱ ፖሊስ በቀጣይ ቀጠሮ የእያንዳንዳቸውን የወንጀል ተሳትፎ ለይቶ የምርመራ መዝገቡንም ይዞ እንዲቀርብ በማዘዝ ለተጨማሪ ምርመራ 10 ቀናትን ፈቅዷል።
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.