የሀገር ውስጥ ዜና

ተጨማሪ 300 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 82 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

By Meseret Demissu

December 15, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 3 ሺህ 867 የላቦራቶሪ ምርመራ 300 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ በፌስ ቡክ ገጻቸው እንደገለጹት 1 ሺህ 82 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት አራት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

እስካሁን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 96 ሺህ 307 ሲደርሱ 1 ሺህ 813 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች 19 ሺህ 420 ሲሆኑ 291 ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

ወረርሽኙ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 714 ሺህ 966 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡