Fana: At a Speed of Life!

ጤና ሚኒስቴር ከሁለት ተቋማት ጋር የአስቸኳይ ሕክምና መመሪያ በጋራ ለመተግበር ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጤና ሚኒስቴር፣ የፌደራል ፖሊስና የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ የአስቸኳይ ሕክምና መመሪያ ለመተግበር ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሰሃረላ አብዱላሂ፣ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፋንታ እና የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ወይዘሮ ወርቅነሽ ብሩ ናቸው የተፈራረሙት።

በስምምነቱ መሰረት የተሽከርካሪ አደጋ የሚደርስባቸው ዜጎች አስቸኳይ ሕክምና የሚያገኙበት ስርዓት ይዘረጋል ተብሏል።

አደጋው የደረሰባቸው ዜጎች እስከ ሁለት ሺህ ብር የሚያስወጣ ሕክምና በነጻ ማግኘት እንደሚችሉ በመመሪያው ተቀምጧል።

የጤና ተቋማት መመሪያውን ስለመተግበራቸው ክትትል እንደሚደረግ በስምምነቱ ላይ ተካቷል።

መድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ ደግሞ ነጻ ሕክምናው ስለመኖሩ ግንዛቤ የሚፈጥሩ ስራዎችን ያከናውናል ነው የተባለው።

የአስቸኳይ ሕክምና አገልግሎቱ ተግባራዊ እንዲሆን ተቋማቱ በቅንጅት የሚሰሩ ሲሆን የክልል ባለድርሻ አካላትም በጉዳዩ ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.