Fana: At a Speed of Life!

777 መወጣጫ ደረጃዎች ያሉት የሀምበርቾ ተራራ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል ከምባታ ጠምባሮ ዞን 777 መወጣጫ ደረጃዎች ያሉት የሀምበርቾ ተራራ ፕሮጀክት ተመረቀ፡፡

የደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ የሀምበርቾ ተራራን ለቱሪዝም ሀብት ለማዋል ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገ ገልጸዋል።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት እንደመሆኑ እነዚህን ሀብቶች በተገቢው መንገድ በማልማት ከዘርፉ በሚገኘው ሀብት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡

አካባቢውን በማልማት ረገድ የዞኑ ህዝብ ያደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

በሀምበርቾ ተራራ ላይ ከሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሀምበርቾ ቱሪዝም እና አረንጓዴ ልማት የመጀመሪያው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የመወጣጫ ደረጃዎቹ መገንባት ከባህር ጠለል በላይ ከ3 ሺህ ሜትር በላይ ከፍታ እንዳለው የሚነገርለትን የሀምበርቾ ተራራን በቀላሉ መውጣት እንደሚያስችል በምረቃ ስነስርአቱ ላይ መጠቀሱን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በምረቃ ፕሮግራሙ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ ሄለን ደበበን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.