Fana: At a Speed of Life!

በሃይሌ ጋርመንት አካባቢ እየተገነባ ያለው የአትክልት ገበያ ማዕከል የግብይት አገልግሎት መስጠት የሚችልበት ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሃይሌ ጋርመንት አካባቢ እየተገነባ ያለው የአትክልት ገበያ ማዕከል የግብይት አገልግሎት መስጠት የሚችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በሃይሌ ጋርመንት አካባቢ በተገነባው የአትክልት ገበያ ማዕከል ተገኝተው በግንባታዉ ስራ ላይ የተሳተፉ ሰራተኞችን እራት ጋበዙ።

የገበያ ማዕከሉ የግብይት አገልግሎት መስጠት የሚችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን አረጋግጠናል ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ በማህበራዊ ገጻቸው እንዳሳወቁት።

የገበያ ማዕከሉ በዚህ ደረጃ ከተያዘለት ጊዜ በፊት በፍጥነት እንዲጠናቀቅ በየዕለቱ ቀን እና ለሊት ለሰራችሁ አመራሮች፣ ሰራተኞች እና ላገዛችሁን የአከባቢው ነዋሪዎች ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ ሲሉም ገልጸዋል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.