Fana: At a Speed of Life!

90 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሀገራቸው ገቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 90 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከሊባኖስ ወደ ሀገራቸው ተመልሱ፡፡

ከመካከላቸውም ዓሥሩ ህጻናቶች መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

ተመላሾቹን ወደ አገራቸ እንዲገቡ ለማድረግ ግሎባል አሊያን ከተሰኘ በኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎች የተመሰረተ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር መፈፀሙን ለማወቅ ተችሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ እና የአለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም(IOM) ተወካይ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት በመገኘት ለተመላሾች አቀባበል አድርገዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.