የሀገር ውስጥ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የዕለት ደራሽ እርዳታ እየቀረበ እንደሚገኝ ተገለጸ

By Meseret Awoke

December 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የዕለት ደራሽ እርዳታ እየቀረበ እንደሚገኝ ተገለጸ።

በክልሉ በመተከል ዞን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የዕለት ደራሽ እርዳታ እየተዳረሰ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በዞኑ በተመረጡ ቦታዎች ማለትም ማንዱራ፣ ጉባ፣ ድባጤ፣ ጋሊሴ፣ ቡለን፣ ዳንጉር እና ወንበራ ላይ ካምፖች ተመስርተው የዕለት ደራሽ እርዳታ በመከፋፈል ላይ እንደሚገኝ የሰላም ሚኒስቴር ገልጿል።