የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር እየመከረ ነው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር እየመከረ መሆኑን ገለጸ፡፡
የምክክር መድረኩ ዋና አላማ በክልሉ የተካሄደው የህግ ማስከበርና በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው ክልሉን መልሶ መገንባት ላይ የወጣቱ ሚና ምን መሆን እንደሚገባው ውይይት ይደረግበታል ተብሏል፡፡
እንዲሁም በትግራይ ክልል የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ላይ ወጣቶች ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል ነው ሌላኛው መሆኑ ተነስቷል፡፡
በአሁኑ ወቅትም የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ፤ የለውጡ ሂደት ውስጥ ትግራይ አካባቢ የነበሩ ክፍተቶች፤ የኢህአዴግ አካሄድ የለውጥ አስፈላጊነት ላይም ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡
የብልጽግና ምስረታና የህወሓት በመጨረሻ ሰዓት ማፈግፈግንና የህወሓት የጸብ ጫሪነትና የለየለት ወንበዴ አካሄድ የተመለከተ ጽሁፍም እየቀረበ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
የውይይት መድረኩ በብልጽግና ወጣቶች ሊግ ምክትል ፕሬዚዳንትና ሌሎች የወጣት ሊጉ አመራሮች እየተመራ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በመነሻ ጽሁፉና በሌሎች ሃገራዊና ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን መነሻ አድርጎ ሰፊ ምክክር እንደሚደረግም ነው ፓርቲው የገለጸው፡፡