Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተወካዮች በድሬዳዋ ከሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተወካዮች በድሬዳዋ ከሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስተባባሪ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉቀን ሃብቶምና የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሁሪያ አሊ ውይይቱን መርተውታል፡፡

በውይይቱ የተሳተፉ የክልሉ ተወላጆች እንደገለጹት የህወሓት ጁንታ ቡድን በትግራይ ያወደማቸውን መሰረተ ልማቶች መልሶ በመገንባት ወደስራ እንዲገባ መደረጉን አድንቀዋል።

“ከሌሎች ብሄር ብሄረሰብ ወንድምና እህቶቻችን ጋር ያለንን አንድነት በማጠናከር በሃገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማምጣት ሃላፊነታችንን እንወጣለን” ሲሉም ተናግረዋል።

በሃገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን ለውጥ ከዳር ለማድረስ እንደሚተጉም አስታውቀዋል።

ውይይቱን የመሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በበኩላቸው የክልሉ ተወላጆች ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በመሆን በክልሉም ሆነ በሃገሪቱ የሰላም፣ የልማትና የትክክለኛ ዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሚያደርገው ክልሉን መልሶ የማደራጀት ሂደት ተወላጆቹ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.