Fana: At a Speed of Life!

በ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የደብረብርሃን አንኮበር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት እየተፋጠነ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 42 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የደብረ ብርሃን አንኮበር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመፋጠን ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

በመንገድ ፕሮጀክቱ የስራ እንቅስቃሴ የአፈር ሙሌትና፣ ድልዳሎ፣ የውሃ መፋሰሻ ቱቦ ቀበራ የሰብ ቤዝ ስራ እንዲሁም የቤዝ ኮርስ ማምረት ስራ እየተካሄደ ይገኛልም ነው የተባለው።

የደብረብርሃን አንኮበር የመንገድ ፕሮጀክት ስራ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ሲሆን ወጪው በመንግስት የሚሸፈን ነው።

በቀጣይ ሶስት ወራት ውስጥም ወደ አስፋልት ንጣፍ ስራ ይሸጋገራል ነው የተባለው።

መስመሩ ከሚያስተናገደው የተሽከርካሪ ብዛት፣ ማህበራዊና ኢኮኖማዊ ፋይዳ አኳያ እንዲሁም ከከተማው ቀጣይ እድገት ጋር አልሞ በአስፋልት ደረጃ እንዲገነባ እየተደረገ መሆኑ ተጠቁሟል።

የፕሮጀክቱ የጎን ስፋት በዞን ከተማ ደብረብርሃን 30 ሜትር ፣ በወረዳ አንኮበር 17 ሜትር በቀበሌ 12 ሜትር ሲሆን በገጠር 10 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ እየተሰራ ነው።

በተጨማሪም ግንባታው በውስጡ የመንገድ አካፋይ፣ እግረኛ መሄጃ እና የመንገድ አቃፊ ትከሻ በግራ እና በቀኝ እንደሚያካትት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.