የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓታት 464 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኘባቸው የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል

By Tibebu Kebede

December 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 451 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 464 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 118 ሺህ 6 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 1 ሺህ 662 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 97 ሺህ 969 ሰዎች  ከቫይረሱ አገግመዋል።

እንዲሀ የ5 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በዚህም ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 818 ደርሷል።

በኢትዮጵያ እስከአሁን ድረስ 1 ሚሊየን 720 ሺህ 417 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓላቸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!