ዓለምአቀፋዊ ዜና

ናይጄሪያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያዋስኗትን ድንበር ዳግም ከፍታለች

By Meseret Demissu

December 17, 2020

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ናይጄሪያ ከቤኒን እና ከኒጀር ጋር የሚያዋስኗትን የድንበር ማቋረጫዎች እንደገና ከፍታለች።

አሁን ላይ የተከፈቱት አራት የድንብር መቋረጫዎች ሲሆኑ በህገ-ወጥ መንገድ ይደረግ የነበረውን የግብርና ምርቶች እና የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለማስቆም በሚል የተዘጋ ነበር፡፡

ሌሎች የድንበር አካባቢዎች በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ እንደገና ይከፈታሉ ነው የተባለው፡፡

ናይጄሪያ ከተወሰነ ጊዜ እምቢተኝነት በኋላ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና አባልነቷን አጽድቃለች ፡፡

ነፃ የንግድ ቀጠና በጥር ወር በይፋ ሥራውን ከጀመረ በዓለም ላይ ሁለተኛው ትልቁ ነፃ የንግድ ቀጠና ይሆናል ነው የተባለው፡፡

ይህም በአፍሪካ ውስጥ ያለውን የንግድ ልውውጥ እሴት በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተመላክቷል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ