Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከሰኞ ጀምሮ የቅድመ መጀመሪያ እና ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የገጽ ለገጽ ትምህርት ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በ4ኛ ዙር የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራ የሚገቡ የክፍል ደረጃዎችን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ይፋ አድርጓል፡፡

የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ደሙ በሰጡት መግለጫ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እየተከላከሉ የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራውን በከተማው ለማስጀመር ውሳኔ ማስቀመጡ ይታወሳል፡፡

በዚህም ከሰኞ ጀምሮ በ4ኛ ዙር በግል ትምህርት ቤቶች የቅድመ መጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች እና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የገጽ ለገጽ ትምህርት ይጀምራሉ ብለዋል፡፡

ህጻናት ተማሪዎች ወደ ገጽ ለገጽ የመማር ማስተማሩ ስራ እየመጡ በመሆኑ የተዘጋጀውን የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን በአግባቡ መተግበር እንዲቻል የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.