Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ ህዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ ህዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ዴኒያ ጋይሌ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ አቶ ደመቀ መንግስት በትግራይ ክልል ስለወሰደው ህግን የማስከበር ዘመቻ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፥ መንግስት ንጹሃንን በጠበቀ መልኩ ዘመቻውን ማከናወኑንም አስረድተዋል፡፡

አያይዘውም የስነ ህዝብ ፈንዱ በሱዳን ላሉት ሴት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ድጋፍ በማድረጉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

መንግስት ህግ የማስከበር ስራውን በፍጥነት አጠናቆ አሁን ላይ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት ስራ እየሰራ መሆኑንም አውስተዋል፡፡

እንዲሁም መንግስት አሁን ላይ በትግራይ ክልል እያደረገ ስላለው ሁሉን አቀፍ ሰብአዊ እርዳታ በተመለከተም ገለጻ አድርገዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ ህዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ዴኒያ ጋይሌ በበኩላቸው፥ ፈንዱ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ሴቶችና ሕፃናት የተጠናከረ ድጋፍ ለመስጠት እንዳቀደ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.