Fana: At a Speed of Life!

እነጃዋር መሀመድ በአቅራቢያችን ችሎት ጉዳያችን ይታይልን ብለው ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የህገመንግስትና የፀረ ሽብር ወንጀሎች ጉዳይ ችሎት የእነ ጃዋር መሀመድን ጉዳይ ዛሬ ተመልክቷል፡፡
ከዚህ በፊት አቶ ጃዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሀምዛ አዳነ እና ሸምሰዲን ጠሀ ባቀረቡት የጽሁፍ አቤቱታ ለደህንነታችን ስለምንሰጋ ችሎቱ በአቅራቢያችን ይሁንልን ሲሉ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡
ይህንን የመረመረው ችሎቱ ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ በዚሁ ችሎት ጉዳያቸው እንዲታይ ፡፡
ለጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ዛሬ አራቱ ተጠርጣሪዎች በችሎቱ ያልተገኙ ሲሆን በመዝገባቸው ስር የተካተቱ ቀሪዎቹ ግን ተገኝተዋል፡፡
ታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.