Fana: At a Speed of Life!

አለም ዓቀፉ የፍልሰት ድርጅት ለሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመረጃ መስጫ ማዕከል ግብዓት የሚያገለግል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ለሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመረጃ መስጫ ማእከል ግብአት የሚያገለግል የገነዘብ መጠኑ ከአንድ ሚሊየን አንድ መቶ አርባ አምስት ሺህ ብር በላይ የሆኑ የተለያዩ ድጋፎችን አበረከተ፡፡
ከተበረከቱት ድጋፎች መካከል ኮምፒውተሮች፣ዘመናዊ ፎቶ ኮፒ ማሽኖች፣ የመረጃ መስጫ ስልኮችንና የተለያዩ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችን ይገኙበታል።
በድጋፍ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን በመወከል ንግግር ያደረጉት የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ብርሃኑ አበራ÷ አለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ከሚኒስቴር መስሪ ቤቱ ጋር በበርካታ ጉዳዮች ላይ በጋራ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም ከአደረጋቸው ድጋፎች መካከል አስራ አንድ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን በመደገፍ ረገድ ያደረገውን አስተዋጽኦ አመስግነው በእለቱ የተከናወነውን ድጋፍ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለታለመለት አላማ እንደሚያውለው ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ በድጋፍ ርክክብ ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የአለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት የፍልሰት አስተዳደር ፕሮግራም አስተባባሪ ማላምቦ ሞንጋ በበኩላቸው÷ ይህ ድጋፍ በዋናነት ለህብረተሰቡ በተለይ በፍልሰት ላይ በቂ መረጃ ማግኘት ለሚፈልግ አካል ሁሉ በቅርበት መረጃዎችን እንዲያገኝ የሚያደረግና የመረጃ ማእከሉን ዘመናዊና የተቀላጠፈ እንዲሆን በማድረግ ረገድ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙ መጠናቀቂያ ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ድጋፍ እየተገነባ የሚገኘውን የመረጃ ማእከል በድጋፍ ስነ-ስርአቱ ላይ ለተገኙ እንግዶች ማስጎብኘቱን ከሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.