Fana: At a Speed of Life!

መንግስት በትግራይ ክልል ለእናቶች፣ ህጻናትና አረጋውያን አልሚ ምግቦችን እያደረሰ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በትግራይ ክልል የመልሶ ማቋቋም ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ የአልሚ ምግብና ሌሎች ሰብአዊ ድጋፎችን በማድረስ ላይ መሆኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

በክልሉ አስቸኳይ የምግብና የህክምና ቁሳቁስ እርዳታዎች ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ካለፉት 10 ቀናት ጀምሮ በመቅረብ ላይ ነው ተብሏል።

በዚህም የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በሽረና ሌሎችም ከተሞች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ስንዴና አልሚ ምግብ እያቀረበ መሆኑ ተገልጿል።

በኮሚሽኑ የአደጋ ምላሽና ክትትል ቡድን መሪ አቶ ታዬ ጌታቸው በሽረ ከተማ ለተፈናቃዮች እየተሰጠ ያለው የሰብዓዊ ድጋፍ በሌሎች ከተሞችም ይቀጥላል ነው ያሉት።

ወደ ክልሉ ከተጓጓዘው ስንዴ ውስጥ ከ18 ሺህ ኩንታል በላይ የሚሆነው መድረሱን ጠቅሰው፥ በዚህም በሶስት ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች እየተከፋፋለ መሆኑን ገልጸዋል።

“በተለይ ለእናቶች፣ ለህጻናት፣ ለህሙማንና ለአረጋውያን የሚሆኑ አልሚ ምግቦችም እየተከፋፈሉ ነው” ብለዋል።

እየተደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ተፈናቃዮቹ በቀጣይ ወደ ቀያቸው ተመልሰው ዘላቂ ህይወታቸውን እንዲጀምሩ መንግስት ሁኔታዎችን እንዲያመቻችላቸው መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.