Fana: At a Speed of Life!

በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ በኤሌክትሪክ አገልግሎት ላይ የደረሱ ጉዳቶችን በመጠገን ወደቀድሞ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኤሌክትሪክ አገልግሎት ላይ የደረሱ የመሰረተ ልማት ጉዳቶችን በመጠገን በአፋጣኝ ወደቀድሞ ለመመለስ እየተሰራ እንዳለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለፀ፡፡

በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት በከተሞቹ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ላይ ፍተሻ በማድረግ የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ፣ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሰረትም በራያ ቆቦ ሮቢትና አላማጣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ላይ ጉብኝት ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ ኃላፊዎች በአማራ እና በትግራይ ሪጅን ስር የሚገኙ የቆቦ፣ ሮቢት እና አላማጣ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ጎብኝተዋል፡፡

በቀጣይም በሌሎች ከተሞች ላይ የደረሱ የመሰረተ ልማት ጉዳቶች ካሉ ከዲስትሪክት እና ማዕከላት ኃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር በጋራ በመቀናጀት አገልግሎት አሰጣጡን በአፋጣኝ መደቀድሞው ለመመለስ የሚሰራ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.