የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት የአባልነት ድርድር የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው

By Abrham Fekede

December 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ንግድ ድርጅት ስምምነት፣ በድርድር አባል የሆኑ ሀገራት ተሞክሮና የኢትዮጵያ የአባልነት ድርድር የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረኩ በአዳማ ከተማ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡

በውይይቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ምክትል አፈ ጉባኤ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ቋሚ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!