Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ ሴት የትምህርት አመራሮች የጋራ ጥምረት ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍ የሴቶች አመራርነት ሀገር አቀፍ ጥምረት ምስረታ በአዲስ አበበ ተካሄዷል።
የጥምረቱ አላማ ሴቶችን ወደ አመራርነት ሊያመጧቸው የሚችሉ ብቃትና ክህሎት እንዲያዳብሩ፣ ውጤታማ የትምህርት ስራ አመራሮች ሆነው እንዲገኙ ማስቻል እንደሆነ ታውቋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ በትምህርት ዘርፍ የሚገኙ ሴቶችን ወደ አመራርነት ማምጣት ሴቶችን ከማብቃት ያለፈ ተጨባጭ ፋይዳ እንዳለው መረዳት ይገባል ብለዋል።
በሀገሪቱ በትምህርት መስክ ሴቶችን በማብቃት ረገድ የተወሰኑ ስራዎች ቢሰሩም ሴቶችን በዘርፉ ወደ አመራርነት ማምጣት የተቻለው 10 በመቶ የሚሞላ እንዳልሆነም ተገልጿል፡፡
በትምህርት መስክ የሚገኙ ሴቶችን ወደ አመራርነት በማምጣት በዘርፉ ሊመዘገቡ የሚገባቸውን ለውጦች ለማስገንዘብ አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ሀገር አቀፍ ጥምረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ነው የተገለጸው።
ጥምረቱ በአሰራር ስርዓት ላይ የሚታየውን ማነቆ ለማለፍና ሴቶች ያላቸውን አቅም ለመጠቀም እንደሚያግዝ መገለፁን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.