Fana: At a Speed of Life!

የአንድሆዴ-አጋምሳ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታን በበጀት ዓመቱ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 88 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የአንድሆዴ-አጋምሳ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታን በተያዝው በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ከአጠቃላይ የመንገዱ ክፍል ውስጥ 71 ኪሎ ሜትሩ አስፋልት የማንጠፍ ስራ ሙሉ ለሙሉ መከናወኑም ተገልጿል፡፡

የመንገዱን ግንባታ በ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ወጪ ጄ.ኤም.ሲ የተሰኘው የሕንድ ዓለም አቀፍ የሥራ ተቋራጭ ድርጅት እያከናወነው ሲሆን ፕሮጀክቱን ለመገንባት የሚውለው ገንዘብ በኢትዮጵያ መንግስት እና ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር የሚሸፈን ይሆናል፡፡

በተያያዘ ዜና የዚሁ የነቀምት – ቡሬ የመንገድ ፕሮጀክት ትስስር አካል የሆኑት ነቀምት-አንድሆዴ ክፍል አንድ እንዲሁም አጋምሳ-ቡሬ ክፍል ሶስት በአጠቃላይ  180 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ ስራ ከዚህ ቀደም ሲያከናውኑ የነበሩ ተቋራጮች በገቡት ውል መሰረት ስራውን ለማከናውን ባለመቻላቸው ውላቸው እንዲቋረጥ ተደርጎ አዲስ ጨረታ እንዲወጣ መደረጉ ይታወሳል፡፡

የጨረታ አሸናፊው የቻይናው ቾንግኪንግ ኢንተርናሽናል ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በአሁኑ ሰዓት የግንባታ ስራውን መጀመሩ ተገልጿል፡፡

የነቀምት-ቡሬ የመንገድ ፕሮጀክት በምሥራቅ ወለጋ ዞን ከምትገኘው ነቀምቴ ከተማ ተነስቶ ደብረ ማርቆስ ባህር ዳር ዋና መንገድ ላይ ከምትገኘው ቡሬ ጋር በቀጥታ ይገናኛል፡፡

ይህም የሃገሪቱን የሰሜንና የምዕራብ ክፍሎች ደረጃውን በጠበቀ የመንገድ መሠረተ ልማት በአቋራጭ ከማገናኘት አንጻር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያበረክታል ነው የተባለው፡፡

ፕሮጀከቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ባለድርሻ አካላት የጎላ ትብብራቸው አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ መቅረቡን ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.