Fana: At a Speed of Life!

ጃንሜዳን ለጥምቀት በዓልና ለወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያነት ዝግጁ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃንሜዳን ለጥምቀት በዓልና ለወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ እና ለልዩ ልዩ ማህበራዊ አገልገሎት ዝግጁ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደረቅ ቆሻሻ ኤጀንሲ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር በዛሬው እለት ጃንሜዳን የማጽዳት ስራ አካሂዷል።

በጽዳት ዘመቻው ከአራዳ፣ ከየካ እና ከጉለሌ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ የጽዳት ሰራተኞች እና በየደረጃው ያሉ አመራሮች ተሳትፈዋል።

የጥምቀት በዓል ማክበሪያና የመጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ የሆነውን ጃንሜዳን ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የማጽዳት ስራ ሲሰሩ መቆየታቸውን የገለጹት ወጣቶቹ በዚህም ደስተኞች መሆናቸውን መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ሐይማኖት ዘለቀ በበኩላቸው ጃንሜንዳን ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ ለመመለስ በፅዳት ባለሙያዎች እና በጎፍቃደኛ ወጣቶች እንዲሁም በአካባቢው ማህበረሰብ ከጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት የፅዳት ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.