የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ቮልካን ቦስኪር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

December 19, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ቮልካን ቦስኪር ጋር ተወያዩ፡፡

አምባሳደር ታዬ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ለፕሬዚዳንቱ ገለፃ አድርገዋል፡፡

በውይይታቸው በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት እና ሌሎች ቀጠናዊ ድርጅቶች አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ እየሰሯቸው ያሉ ስራዎች ላይም ማብራያ ሰጥተዋል፡፡

የኮቪድ ክትባትን ለአፍሪካ ሀገራት ለማድረስ የተቀናጀ ትብብር እንደሚያስፈልግ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ለ75ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ቮልካን ቦስኪር አብራርተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!