Fana: At a Speed of Life!

መንግስት በህግ ማስከበር ዘመቻው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም ከሱዳን ጋር በትብብር እንደሚሰራ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በህግ ማስከበር ዘመቻው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስና ለማቋቋም ከሱዳን ጋር በትብብር እንደሚሰራ በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ገለጹ፡፡

አምባሳደሩ ከአል ዓረቢያ አልሃዳጥ ቴሌቪዥን ጋር በትግራይ ክልል ስለተወሰደው የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ ዙሪያ ቆይታ አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም የህወሓት ጁንታ ያሉትን ልዩነቶች እንዲፈታ የቀረቡለትን በርካታ አማራጮች ውድቅ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አውስተው ድርጊቱ መንግስት የሃገርን ሉዓዊነት ለማስከበር ወደ ህግ ማስከበር ዘመቻው እንዳስገባውም አብራርተዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ሲካሄደ የቆየው ህግን የማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን በመጥቀስ፥ አሁን ላይ የጁንታውን ቡድን አባላት የማደን ተግባር እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ መገንባት እና ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረግ የመንግስት ዋነኛ ትኩረት እንደሆነ መናገራቸውንብ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም በህግ ማስከበር ዘመቻው ሳቢያ ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው በማምጣት መልሶ ለማቋቋም መንግስት ከሱዳን ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.