Fana: At a Speed of Life!

“እኔም ለመከላከያ ሰራዊት እሮጣለው” በሚል መሪ ቃል በሀረር ከተማ የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “እኔም ለመከላከያ ሰራዊት እሮጣለው” በሚል መሪ ቃል በሀረር ከተማ ከ3 ሺህ በላይ ተወዳዳሪ ስፖርተኞችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ፡፡

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን እና በሀረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በጋራ ባዘጋጁት የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ከሀረሪ ክልልና ከምስራቅ ሐረርጌ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

መከላከያ ሰራዊቱ በጁንታው ህውሃት ቡድን ላይ ባከናወነው ህግን የማስከበር ዘመቻ ላይ አኩሪ ድል በማስመዝገቡ ለማመስገንና ለመከላለያ ሠራዊት ያለውን አጋርነት ለማሳየት በተከናወነው የጎዳና ላይ ሩጫ  ውድድር ላይ ከፍተኛ የሀረሪ ክልልና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ አመራር አካላት ተገኝተዋል፡፡

መነሻና መድረሻውን ሀረር ራስ መኮንን አደባባይ ያደረገውን የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የኦሮምያ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮምሽነር ናስር ሁሴን እና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሁሴን ፈይሶ አስጀምረዋል::

በዚሁ ወቅት የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሁሴን ፈይሶ እንደተናገሩት ጁንታው የህውሃት ቡድን አገሪቱንና ህዝቡን ለማተራመስና ለውጡን ለመቀልበስ ያልሞከረው ጥረት እንዳልነበርና በመጨረሻም በሰሜን ዕዝ ላይ በፈፀመው ግፍ የተሞላበት ድርጊት ሳቢያ  ሰራዊቱ ባደረገው ህግን የማስከበር ዘመቻ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመደምሰሱ በተገኘው ድል ደስታ ለመግለጽ የተዘጋጀ የሩጫ ውድድር መሆኑን አስታውቀዋል።

የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሩ ዋና ዓለማ የመከላከያ ሰራዊቱ በጁንታው የህውሃት ቡድን ላይ በወሰደው ህግ የማስከበር ዘመቻ የተገኘውን አኩሪ ገድል ለመዘከር መዘጋጀቱን ነው የኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ናስር ጠቁመው እንዲህ ዓይነት መሰል የስፖርት ውድድሮች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል::

በውድድሩም በሁለቱም ፆታዎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ አሸናፊዎች የተዘጋጀላቸውን የሜዳልያ ሽልማት ከዕለቱ ክብር እንግዶች እጅ ተቀብለዋል::

በተሾመ ኃይሉ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.