Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አና አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በውጭ ቋንቋዎች ከሚጽፉ የሚዲያ ባለሙያዎችና የማህበረሰብ አንቂዎች ጋር ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በውጭ ቋንቋዎች ከሚጽፉ የሚዲያ ባለሙያዎችና የማህበረሰብ አንቂዎች ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ በእንግሊዝኛ፣ በአረብኛ፣ በፈረንሳይኛ እና በሃገር ውስጥ ቋንቋዎች በሚዲያ እና በድረ ገጽ ከሚጽፉ ተንታኞች እና ከማህበረሰብ አንቂዎች ጋር ውይይት ተካሄዷል።

ውይይቱ በወቅታዊ ሃገራዊ ሁኔታና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተጠቁሟል።

አምባሳደር ሬድዋን በውይይቱ በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅትም በናይል ወንዝ ላይ የጋራ ተጠቃሚነት፥ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እና የሶስትዮሽ ድርድር የመወያያ ርዕሶች መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የታችኞቹ የናይል ተፋሰስ ሃገራት በድርድሩ ላይ የሚከተሉት ጂኦፖለቲካዊ አንድምታ ላይም አምባሳደር ሬድዋን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ ላይ የሚደርሰውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመመከት ከዜጎች የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ የጠቆሙት ሚኒስትር ዲኤታው፣ በተለይ የማህበረሰብ አንቂዎች ሃገራዊ ፈተናዎችን ለመቋቋም እና ሃገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚኖራቸውን ከፍተኛ ድርሻ በመገንዘብ ከትናንሽ አጃንዳዎች መውጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

በዋና ዋና ሃገራዊ አጃንዳዎች ዙሪያ በማተኮር መግባባትን ለመፍጠር፣ የማህበረሰቦችን አብሮነት ማጠከር እና የባዕዳን እኩይ አጃንዳዎችን ማክሸፍ እንደሚገም በአጽንኦት ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው የማህበረሰብ አንቂዎች መንግሥት ነቅቶ ኃላፊነቱን እንዲወጣ በማድረግ ብሄራዊ ጥቅሞች እንዲከበሩ፣ የህዝቦች አብሮነትና ወንድማማችነት ስሜት እንዲገነባ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.