Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 469 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 1294 ሰዎች አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ተጨማሪ 469 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 1294 ሰዎች አገግመዋል።

የጤና ሚኒስቴር ባወጣው እለታዊ መግለጫ ለ6 ሺህ 313 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 469 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

እስካሁንም ለ1 ሚሊየን 738 ሺህ 290 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

በዚህም በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 119 ሺህ 494 ደርሷል።

በትናንትናው ዕለት 1 ሺህ 294 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም 102 ሺህ 153 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

በተያያዘም ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ የሶስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ይህን ተከትሎም 1 ሺህ 846 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 1 ሺህ 5493 ሰዎች መካከል 258 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ ናቸው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.