የሀገር ውስጥ ዜና

ላለፉት 30 አመታት አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው በነበሩ የደርግ ባለስልጣናት ላይ ተላልፎ የነበረው የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተሻሻለ

By Tibebu Kebede

December 20, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ላለፉት 30 አመታት አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው በነበሩት የደርግ ባለስልጣናት ላይ ተላልፎ የነበረው የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተሻሻለ፡፡

ማሻሻያውንም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በፊርማቸው አጽድቀዋል፡፡

ማሻሻያው የጸደቀላቸው ለሌተናል ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህና ሌተናል ጄኔራል አዲስ ተድላ ናቸው።

በቀድሞዎቹ ባለስልጣናት ላይ ተላልፎ የነበረው የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተሻሽሎላቸዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!