የሀገር ውስጥ ዜና

ወጣቶች የዲጂታል እውቀት እንዲኖራቸው ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ

By Tibebu Kebede

December 21, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር “የጤና ጉዞ ወደ ኪቢቃሎ ተራራ” በሚል ለወጣቶች የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን አስተዋወቀ።

ትውውቁ በወልዲያ ከተማ ተራራ ላይ በተደረው ጉዞ ላይ ለተሳተፉ ወጣቶች የተደረገ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አህመዲን መሀመድ ለቴክኖሎጂ ቅርብ የሆነውን ወጣት የዲጂታል እውቀት እንዲኖረው ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል።

አብዛኛዎቹ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ በመሆናቸው ዲጂታል እውቀት በመጨመር ቴክኖሎጂን ለጤና፣ ለንግድ እናለመልካም ነገር እንዲያውሉት ጠይቀዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ከደሴ ኮምቦልቻ ጉዞ በማድረግ የተጀመረው የእግር ጉዞ ሰባተኛው ዙር ወደ ኪቢቃሎ ተራራ የተደረገ ሲሆን ከኮምቦልቻ እስከ ደሴ ያሉ ወጣቶች ተሳትፈዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን በተለያዩ አካባቢዎች እያስተዋወቀ ይገኛል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!