Fana: At a Speed of Life!

በጣና ሃይቅ ዙሪያ ግንባታቸው የተጠናቀቀና በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በጣና ሃይቅ ዙሪያ ግንባታቸው የተጠናቀቀና በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ርክክብና ግንባታው ሊፋጠን በሚችልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

በውይይቱ ላይ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት የተጠናቀቀው የመገጭ ሰራባ መስኖ ልማት ፕሮጀክት፣ መገጭ ግድብ ግንባታና የርብ መስኖ መሬት ዝግጅት ፕሮጀክቶች ትኩረት ተደርጎባቸዋል፡፡

የተጠናቀቀው የመገጭ ሰራባ መስኖ ልማት ፕሮጀክት እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓም ድረስ ኤሌክትሪክ እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ 4 ሺህ 40 ሄክታር የማልማት አቅም ያለውና ከ6 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ለግንባታው 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡

በ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በመገንባት ላይ የሚገኘው የመገጭ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት እስከ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 69 በመቶ የደረሰ ሲሆን በተያዘው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙም ነው የተገለጸው፡፡

እንዲሁም የርብ መስኖ መሬት ዝግጅት ፕሮጀክት እስከ ህዳር 30 ቀን 2013 ድረስ ግንባታው 79 በመቶ የደረሰ ሲሆን የቀድሞው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን በራሱ ፍቃድ በማቋረጡ በ15 ቀናት ውስጥ ለሌላ ተቋራጭ እንዲሰጥ መወሰኑን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ብዙነህ ቶልቻ አስታውቀዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.