Fana: At a Speed of Life!

ሃገር አቀፍ የፀረ ሙስና ንቅናቄ መድረክ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው

ሃገር አቀፍ የፀረ ሙስና ንቅናቄ መድረክ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃገር አቀፍ የፀረ ሙስና የንቅናቄ መድረክ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

መድረኩ ፌደራል የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተዘጋጀ ነው፡፡

በመድረኩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

የንቅናቄ መድረኩ የትውልድን ስነምግባር በማጠናከር፣ በስነስርዓት በመምራት፣ የሌብነትና ብልሹ አሰራርን በመታገል የብልጽግና ጉዟችንን እናፋጥናለን በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ታገሰ ጫፎ በኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ እየታየ የሚገኘው የስነ ምግባር ዝቅጠት፣ ሙስና እና ሌብነት ትውልድ ላይ ቀደም ብሎ ባለመሰራቱ የመጣ አሉታዊ ተጽዕኖ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም የስነምግባር ግንባታው ዋነኛ ትኩረት ከመዋዕለ ህጻናት እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊሰራበት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው በተለይ የህወሓት የጁንታ ቡድን በተደመሰሰበት ማግስት ሃገራዊ ንቅናቄው መካሄዱ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

አያይዘውም ቡድኑ በተቀናጀ መልኩ የሙስና ተግባርና ብልሹ አሰራርን እንደሀገር አስፋፍቶ ህዝቡን ድህነት ውስጥ መክተቱን በመድረኩ ላይ አንስተዋል፡፡

ለዘመናት በሀገሪቱ ፈተና የነበረው ይህ ቡድን አልጠግብ ባይነቱ እያየለ በመምጣቱ በሀገሪቱ ስር የሰደደ ሌብነት እና ሙስና ተስፋፍቶ መቆየቱንም ነው የገለጹት፡፡

አክለውም ትውልዱን በመልካም ስነምግባር መገንባት ያለባቸው የትምህርት፣ የሃይማኖት፣ የመንግስት፣ የሲቪል ተቋማት እና መገናኛ ብዙኃን ሃገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የፌደራል ስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽነር አቶ ጸጋዬ አራጌ ሙስናን ለመታገል ህዝቡ በጸረ ሙስና ትግሉ ሚናውን እንዲወጣ የሚያነቃቁ ተጨማሪ መድረኮች በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የሙስና አስከፊነት እና ሀገር አፍራሽነትን የሚያስረዱ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች በምሁራን ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

 

በጳውሎስ አየለ እና አዳነ በፍቃዱ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.