Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ የአቪዬሽን ደህንነት ኤጀንሲ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ የአቪዬሽን ደህንነት ኤጀንሲ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ዳግም እንዲበር ፈቃድ ሰጠ፡፡
የአውሮፓ የአቪዬሽን ደህንነት ኤጀንሲ ሃላፊ÷ የቦይንግ 737 ማክስ አሁን ለመብረር ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኤጀንሲው ከአምራቹ ጋር ጥብቅ ፍተሻና ምርመራ መደረጉን በመጥቀስም አሁን ላይ አውሮፕላኖቹም ለበረራ ዝግጁ እንደሆኑ ተረጋግጠዋል ብለዋል፡፡
በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ሁለት አደጋዎች ከተከሰቱ በኋላ ባለፈው አመት መጋቢት ወር ላይ በረራ ማቋረጡ ይታወሳል፡፡
የአውሮፕላኑ የመጀመሪያ አደጋ በፈረንጆቹ ጥቅምት ወር 2018 ሲሆን÷ 188 ሰዎችን የያዘው የላየን ኤር ቦይንግ 737 የመንገደኞች አውሮፕላን መከስከሱ የሚታወስ ነው።
ከዚያ በኋላ ደግሞ መጋቢት ወር መጀመሪያ 2019 ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን 157 ሰዎችን ይዞ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በመብረር ላይ እያለ ቢሾፍቱ መከስከሱም ይታወቃል።
ከዚያን ጊዜ ወዲህ በረራ ያቋረጠ ሲሆን የተለያዩ ማሻሻያዎች እና ሙከራዎችን ሲደርግ ቆይቷል፡፡
አሁን ላይ የአውሮፓ የአቪዬሽን ደህንነት ኤጀንሲ የቦይንግ 737 ማክስ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን አስታውቋል፡፡
አውሮፕላኖቹ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ በረራ ይመለሳሉ የተባለ ሲሆን ከዛ በፊት ግን ተጨማሪ ሙከራዎች እንደሚያደርጉም ነው የተነገረው፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.