Fana: At a Speed of Life!

ኮሎኔል ይርጋለም ፍቃዱ እና ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ ብርሃን ሊሸሹ ሲሉ አፋር ላይ መያዛቸውን መርመሪ ፖሊስ ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ኮሎኔል ይርጋለም ፍቃዱ እና ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ ብርሃን ሊሸሹ ሲሉ አፋር ላይ መያዛቸውን መርመሪ ፖሊስ ለችሎት ገለፀ።
ይህን የገለጸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ አባል ተጠርጣሪዎቹ በዋስ እንዲወጡ ፍርድቤቱን መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ 2ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት እነዚህ ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ 10 የመከላከያ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተመድበው ሲሰሩ የነበሩ መኮንኖችን ጉዳይ ተመልክቷል።
ተጠርጣሪዎቹ ኮሎኔል ሃረጎት በርሄ፤ሌተናል ኮሎኔል ሙሉ አለሙ፤ብርጋዴል ጄኔራል ይልማ ከበደ ፤ኮሎኔል በረከት ወልደአብየዝጊ ፤መቶአለቃ ገብረጎርጊስ፤ ሌቴናል ኮሎኔል ግደይ ገብረእየሱስ፤ሻለቃ ሃሳቡ መሃመድ ፤መቶአለቃ ጸሃየ ሃይሉ፤ኮሎኔል ይርጋለም ፍቃዱ እና ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ ብርሃነ ናቸው።
ተጠርጣሪዎቹ በመከላከያ ሰራዊት በስራላይ ሆነው ለወንጀል መፈጸም የስራ ክፍፍል አድርገው ሲሰሩ እንደነበር በማስረጃ አረጋግጫለው ሲል መርመሪ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ የሰራውን ስራ ለችሎት ገልጿል።
ውጭ ሃገር ላሉ አካላት ሃሰተኛ መረጃ ሲያቀብሉ ነበር ያለው መርማሪ ፖሊስ በወቅቱም በመከላከያ ሰራዊት ችግር እንዲስፋፋ ሲያባብሱ ነበር ብሏል ፖሊስ ለችሎቱ።
በዚህ ተሳትፏቸውም በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ሲሰሩ እንደነበር ባገኘሁት ማስረጃ አረጋግጫለው ሲል ተናግሯል።
ተጠርጣሪዎቹ በተለያዩ ቦታዎች በስራ ላይ እንደነበሩ ገልጸው ÷የወንጀል ተሳትፏችን ሊገለጽ ይገባል ፤ከወንጀሉ ጋር ገንኙነት የለንም ሲሉ በነጻ አለያም በዋስ እንዲወጡ ችሎቱን ጠይቀዋል።
መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ኮሎኔል ይርጋለም ፍቃዱ እና ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ ብርሃን ሊሸሹ ሲሉ አፋር ላይ መያዛቸውን ለችሎት ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ቡድኖቻቸው ግብረአበሮቻቸው ስላሉ ከዚህ ቢወጡ ጉዳት ሊያደርሱና ሊሸሹም ይችላሉ ሲል ዋስትናውን ተቃውሞ ተከራክሯል።
የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው ችሎቱ የእያንዳንዳቸውን ተሳትፎ ከመዝገቡ ተመልክቶ ትዛዝ ለመስጠት ለታህሳስ 15 ቀን 2013 አ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.