Fana: At a Speed of Life!

ከ389 ዓመት በኋላ በተከሰተው የጁፒተር እና ሳተርን ተፈጥሯዊ ጥምረት ትዕይንት ላይ ያተኮረ ፕሮግራም ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ከ389 ዓመት በኋላ በተከሰተው የጁፒተር እና ሳተርን ተፈጥሯዊ ጥምረትና የህዋ ላይ ትዕይንት የግንዛቤ መፍጠሪያ ፕሮግራም ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
ዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ የሚከሰተውን የጁፒተር እና ሳተርን ተፈጥሯዊ ጥምረት በቴሌስኮፕ የማሳየት እና ስለህዋ ሳይንስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡
ፕሮግራሙን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሣይቲ እና የአንድሮሜዳ ፕሮግራም ናቸው፡፡
ሁለቱ ታላላቅ ፕላኔቶች በ0.1 ዲግሪ ተቀራርበው የሚታዩበት ትዕይንት መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
የሁለቱ ፕላኔቶች እንደዚህ አይነት አጭር ቅርርብ ከ389 ዓመት በኋላ የተከሰተ መሆኑን በኢፌዴሪ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላመከው መረጃ አሳውቋል፡፡
ይህንን ተፈጥሯዊ ክስተት ለህብረተሰቡ ለማሳየት ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም በቤልቩ ሆቴል ከ11፡30 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት የሚቆይ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.