የሀገር ውስጥ ዜና

ህወሃት አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤውን ሊያካሂድ ነው

By Tibebu Kebede

January 03, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ህወሃት አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤውን ታህሳስ 25 እና 26 ቀን በመቐለ ከተማ ሊያካሂድ ነው፡፡

ድርጅቱ በሚያካሄደው ጉባኤ የኢህአዴግን ውህደት በሚመለከት ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ በትናትናው ዕለት በሰጠው መግለጫ÷ አስቸኳይ ጉባኤውን የሚያስተባብር  አዘጋጅ ኮሚቴ በማቋቋም አስፈላጊውን ዝግጅት ሲያካሂድ መቆየቱን ነው የገለፀው፡፡

በጉባኤው ከህወሃት መሰረታዊ ድርጅቶች የተወከሉ አባላት ፣ ምሁራን ፣ የሀይማኖት መሪዎች ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሏል፡፡