Fana: At a Speed of Life!

ከ39 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖቶች የተገኘባቸው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በሰንበቴ ከተማ ከ39 ሺህ ብር በላይ ባለ 200 ሀሰተኛ የብር ኖቶች የተገኘባቸው ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሃመድ አሊ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ተጠርጣሪዎቹ በትናንትናው እለት ሁለት ሠንጋዎችን በ29 ሺህ 400 ብር በመግዛት ከፍለው ሊሄዱ ሲሉ ሻጮች ብሩን በመጠራጠራቸው ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠታቸው ሊደረስባቸው ችሏል።

ፖሊስም ባደረገው የማጣራት ሥራ ብሩ ሃሰተኛ መሆኑን በማረጋገጡ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር በማዋል ባደረገው ፍተሻ ተጨማሪ 10 ሺህ ሃሰተኛ የብር ኖት ማገኘቱን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።

ከአንድ ወር በፊትም 6 ሺህ ሐሰተኛ ባለ 200 የብር ኖቶች በመያዝ ህብረተሰቡን ለማጭበርበር የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉንም አስታውሰዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.