Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር አይሮሪት ከኦማን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ጸሃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር አይሮሪት መሐመድ ከኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማቲክ ዘርፍ ምክትል ጸሃፊ ኻሊፋ ቢን አሊ ቢን ኢሳ አልሃርቲ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅትም አምባሳደር አይሮሪት በሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለጻ አድርገዋል።
ከዚያም ባለፈ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የኢኮኖሚ ውህደት እየተጫወተች ስላለው ሚና አስረድተዋል።
ከዚያም በላፈ ሀላፊዎቹ በኢትዮጵያ እና በኦማን መካከል ያለውን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት በተለይም በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እንዲሁም በሠራተኛ ልውውጥ ጉዳዮች ላይ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ኦማን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.