Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የባለድርሻ አካላትና ሴክተር መስርያ ቤቶች ሚና እና ቅንጅታዊ ስራዎች ዳግም መጠናከር እንደሚገባ ቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የባለድርሻ አካላትና ሴክተር መስርያ ቤቶች ሚና እና ቅንጅታዊ ስራዎች ዳግም መጠናከር እንደሚገባቸው ተገለጸ።
ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዳግም ትኩረት ተሰጥቶት የመስራት አስፈላጊነት ዙርያ ምክክርና ውይይት ተካሂዷል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ÷ የኮሮና ቫይረስ ወደ አገራችን ከመግባቱ በፊትና ከገባ በኃላ የተሰራው ቀንጅታዊ ስራዎች ጠንካራ እንደነበሩና በዚህም በሽታው ሊያስከትል የሚችለውን የከፋ ጉዳት መቀነስ እንደተቻለ አብራርተዋል፡፡
ዶክተር ሊያ አያይዘውም የሴክተሮች የተቀናጀ እና በተቋማቸው ላይ ሲተገብሯቸው የነበሩት በሽታውን የመከላከያ መንገዶች እንቅስቀሴ አሁን ላይ እየተቀዛቀዘና እየቀነሰ እንደመጣ እና በአንጻሩ ደግሞ የበሽታው ስርጭትትና የሚያስከትለው ጉዳት እየጨመረ መምጣቱትን አስረድተዋል።
በቀጣይም የሴክተሮችና ባለድርሻ አካላት የትብብር ስራዎች ካልተጠናከሩ በ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችልም ጭምር ስጋታቸውን ጠቁመዋል፡፡
የጤና ሚኒስተር ዴኤታ ወይዘሮ ሰዓረላ አብዱላሂ በበኩላቸው ÷ባለፉት ጊዜያት በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች ውጤቶች እንደተገኙ አስታውሰዋል።
አሁን ላይ ግን እንደ ግለሰብም ፣ እንደተቋምም የሚስተዋለው ቸልተኝነትና መዘናጋት የሚያስከትለው ሁለንተናዊ ጉዳት ከባድ ሊሆን ስለሚችል የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመርያ ተግባራዊ በማድረግ በኩል ተቋማዊና ቅንጅታዊ ስራዎች መጠናከር አለባቸው ብለዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎችም ባነሷቸው ሀሳቦች አሁን ላይ ቅንጅታዊ አሰራሮች መቀነሳቸውን ገልጸው÷ ችግሩ ዳግም ትኩረት እንደሚያስፈልገውና በክትትል እንዲሁም በቁጥጥር የታገዘ እስከ ታችኛው መዋቅር ድርስ ስርዓት ተዘርግቶለት ሊሰራ እንደሚገባና ለዚህም ሚናቸውን እንደሚወጡ በውይይቱ ላይ አንስተዋል፡፡
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አሁናዊ መረጃዎች ፣ በመሰራት ላይ እና የታቀዱ ዝዝርዝር ስራዎችን የተመለከተም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.