Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከዚህ ቀደም በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ተሳትፎ ያደረጉ 711 አመራሮች ከሀላፊነት ተነስተዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ከዚህ ቀደም በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ተሳትፎ ያደረጉ 711 አመራሮች ከሀላፊነት መነሳታቸውን የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሰናይት ሰለሞን አስታወቁ፡፡

ሃላፊዋ በክልሉ የተካሄደውን የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በክልሉ በጉራፈርዳ፣ በወላይታ፣ በኮንሶ ዞን እና በዙሪያው ባሉ ልዩ ወረዳዎች የአደረጃጀት እና የወሰን ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ የህዝቡን ጥያቄዎች በሀይል ማስፈጸም ይቻላል በማለት የህወሓት ጁንታ ለግጭት አመቺ የሆኑ ቦታዎችን በመጠቀም ህብረተሰቡ ያልተገባ ዋጋ እንዲከፍል ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

በብዝሀነቱ የሚታወቅና ለሌሎች አካባቢዎችም ተምሳሌት የሆነውን የደቡብ ክልል ጽንፈኛው የህወሓት ጁንታ ሀይል ለእኩይ አላማ ሲጠቀምበት እንደነበርም በዝርዝር መገምገሙን ነው የተናገሩት፡፡

ጽንፈኛው ቡድን ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ሀብት በመመደብ ሲንቀሳቀስ መቆየቱንም አብራርተዋል፡፡

በተፈጠረው ችግር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጃቸው መኖሩ የተረጋገጠ 711 አመራሮች ከሀላፊነት እንዲነሱ ሲደረግ፤ 918 የሚሆኑት ደግሞ ከቦታቸው እንዲሸጋሸጉ ተደርጓልም ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም 1 ሺህ 966ቱ ደግሞ በማስጠንቀቂያ መታለፋቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.