Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ 7ኛ መደበኛ ስብሰባውን በነገው ዕለት ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013(ኤፍቢሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 5ኛው ምክር ቤት በ6ኛው የሥራ ዘመኑ 7ኛውን መደበኛ ስብሰባ በነገው ዕለት በአምስት የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ያካሄዳል፡፡

ከአጀንዳዎች አንዱ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የቦርድ አባላትን እንደገና ለማደራጀት የቀረበውን የቦርድ አባላት ሹመት መርምሮ ማጽደቅ ሲሆን፤ የዕለቱ 2ኛ አጀንዳ ይሆናል ተብሏል፡፡

በምክር ቤቱ የአሠራር እና የአባላት ስነ-ምግባር ደንብ አንቀጽ 92 መሠረት፤ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች በቃል የሚሰጡት መልስ የሚደመጥበት 5ኛው እና የመጨረሻው አጀንዳ፤ በነገው ስብሰባ ያተኩራል፡፡

በ3ኛ እና በ4ኛ አጀንዳነት የሚቀርቡት የመገናኛ ብዙኀን ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያን እንደገና ለማሻሻል የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መምራት የነገው ስብሰባ አካል ናቸውም ነው የተባለው፡፡

አጀንዳ ቁጥር 1 ሆኖ የሚቀርበው ደግሞ የምክር ቤቱን 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.