Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ 355 ተሽከርካሪዎችን ለዞን እና ወረዳዎች አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር 355 ተሽከርካሪዎችን ለሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች አስረከቡ፡፡

በዚህ ወቅትም ተሽከርካሪዎቹ በክልሉ የጸጥታ መዋቅሩን ለማጠናከር የሚኖራቸው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተሽከርካሪዎቹ በክልሉ ለሁሉም ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች እና ወረዳዎች የሚከፋፈሉ ይሆናል ብለዋል፡፡

በግዢ ከቀረቡት ተሽከርካሪዎች ውስጥ 46 ያህሉ ለሲዳማ ክልል የሚሰጡ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በውስን በጀት የተገዙትን ተሽከርካሪዎች በጥንቃቄ መያዝ እንደሚገባ መናገራቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.