Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮቿን በራሷ የመምራትና ህግና ስርዓት የማስፈን መብት ያላት ሀገር ናት -የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁለቱ ፓርቲዎች አመራሮች በቀጣይ የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነቱን አጠናክረው ስለሚቀጥሉበት ጉዳይ በበይነ መረብ ውይይት አካሄደዋል፡፡

ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ የተለያዩ ስኬታማ ልምዶች ያለው ፓርቲ እንደሆነ ገልጸው፤ የብልጽግና ፓርቲ የጀመረውን ሁለንተናዊ ሪፎርም ለማጠናከርና ውጤታማ ለማድረግ ከቻይና ፓርቲ ተሞክሮዎችን የመቅሰም ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የህግ ማስከበር ስራ ላይ እንደነበረችና የህግ ማስከበሩ እንደተጠናቀቀ ለቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ አመራሮች ዶክተር ቢቂላ ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል የነበረው የህግ ማስከበር ስራ በመጠናቀቁ የትግራይ ህዝብ ወደ ሰላማዊ የእለት ከእለት እንቅስቃሴው የተመለሰ ሲሆን በሀገሪቱ በ2013 ዓ.ም ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ በብልጽግና ፓርቲ በኩል እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶችን አስረድተዋል፡፡

በውይይቱ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ተገኝተው የኢትዮጵያንና የቻይናን ቆየት ያለ ወዳጅነት አብራርተዋል፡፡

አምባሳደሩ ኢትዮጵያና ቻይና ስትራቴጅካዊ ወዳጆች እንደሆኑ ጠቅሰው ሃገሪቱ በብዙ ዘርፍ እንደተጠቀመችም ነው የገለጹት፡፡

ሁለቱ ሀገራት በአሁኑ ወቅት በበርካታ ጉዳዮች ላይ አብረው እየሰሩ እንደሚገኙም ነው አምባሳደሩ ያነሱት።

የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲን በወከል በውይይቱ የተገኙት የአፍሪካ ጉዳዮች ጄኔራል ዳይሬክተር ዋንግ ሂሚንግ የብልጽግናና የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል የፓርቲያቸው ፍላጎት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ በተለይም ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጋር ቻይና ለምታደርገው ግንኙነት ኢትዮጵያን እንደ ማእከል እንደሚጠቀሙ ጠቁመዋል።

ለዚህም ኢትዮጵያን እየመራት ከሚገኘው የብልጽግና ፓርቲ ጋር ጠንካራ ግንኙነት መመስረት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ፍላጎት ነው ብለዋል፡፡

ቻይና በየትኛውም ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት ፍላጎት እንደሌላት የገለጹት ዋንግ ሂሚንግ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮቿን በራሷ የመምራትና ህግና ስርዓት የማስፈን መብት ያላት ሀገር መሆኗን አብራርተዋል፡፡

የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ብልጽግና ፓርቲ ለሚያካሂዳቸው የፓርቲ ሪፎርም ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋልም ነው ያሉት፡፡

የብልጽግና እና የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ግንኙነታቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ያስችላቸው ዘንድ በቅርቡ የመግባቢያ ሰነድ ይፈራረማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.