Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት መስራች ጉባኤ በሀዋሳ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት መስራች ጉባኤ በሀዋሳ ተካሄደ።

በጉባኤው ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳየች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በጉባኤው የክልሉ ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ክልላዊ ምክር ቤት አደረጃጀትና አመራር ረቂቅ መመሪያ አፀድቋል።

በውይይቱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የከተማ ስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጄንሲ ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ቡልቻ በቀረበው ረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየት ተሰጥቶበት እንዲፀድቅ በጠየቁት መሰረት በጉባኤው ተሳታፊዎች እና በክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላት አስተያየት ተሰጥቶበት የቀረበው ረቂቅ መመሪያ በጉባኤተኞች እንዲጸድቅ ተደርጓል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.