Fana: At a Speed of Life!

በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲያካሂድ የቆየው ብሄራዊ የማህበረሰብ ተኮር የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲያካሂድ የቆየው ብሄራዊ የማህበረሰብ ተኮር የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ።

በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ የሰላም ሚኒስትር  ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካልሚል እንደተናገሩት በአንድ ሀገር ዘላቂ ሰላም ግንባታና ብሄራዊ መግባባት ህብረተሰቡ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተኮር የሆነ የምክክር መድረክ መዘጋጀት የሚከሰቱ ችግሮች ምንጫቸው ምን እንደሆነ ለመረዳተ ያግዛል ተብሎ በመታመኑ ነው ብለዋል፡፡

˝አሁን የምንገኝበት ምዕራፍ በጆሮ መስማት ሳይሆን በልብ ማድመጥን የሚጠይቀን ወቅት ላይ ነን˝ ያሉት ሚኒስትሯ ልብ በልብ በመደማመጥ አንዱ የቸገረውን ሌላው በመረዳት በጋራ መፍትሄዎችን ለመፍጠር እንደዚህ አይነቱ የምክክር መድረክ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ነው ያሉት፡፡

ከዚህ መድረክም ህዝቡ በሰላም ግንባታና ብሄራዊ  መግባባት ላይ የሚለውን በማዳመጥ ግብዓቶችን በመውሰድ ስራዎች እንደሚከፋፈሉ መናገራውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያሊኖራት የሚገባት ስፍራ ላይ እንድትሆን ሁሉም በመቀናጀትና  በመተባበር የሀገሪቱን ሰላም ለማረጋገጥ የበኩሉን አስተዋፆ ሊያበረክት ይገባል በማለት በመላ ሀገሪቱ በውይይቱ ለተሳተፉ የማህበረሰብ አካላት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.