Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን በንፁሃን ላይ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን በንፁሃን ላይ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፈ አቶ መለሰ በየነ አስታወቁ።

በተፈፀመው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ህይወታቸው ካለፈው ባሻገር የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት ማጋጠሙን ገልፀዋል።

የጉዳቱ መጠኑ እየተጣራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በርካታ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸው እና ንብረት መውደሙን ከአካባቢው የደረሳቸው መረጃ እንደሚያመለክት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በአጠቃላይ የደረሰውን ጉዳት መረጃዎችን በማጥራት የክልሉ መንግስት ለህብረተሰቡ እንደሚያደርስም ነው የተናገሩት።

በትናንትናው ዕለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በነበረው ውይይት ጥቃቶችን ለአንድ ጊዜ እና ለመጨረሻ ጊዜ ማስቆም ይገባል የሚል አቅጣጫ መቀመጡን አብራርተዋል።

በእነዚህ ጥቃቶች በተለያዩ መንገድ እጃቸው ያለበትን አመራሮችም ሆነ ማንኛውም አካል ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብለዋል።

ህብረተሰቡን የማረጋጋት ስራ እየተከናወነ ሲሆን ጥቃቱ ከተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ የመከላከያ ሰራዊት፣ የክልሉ የፀጥታ ሀይልና ሚሊሻዎች በአካባቢው በመሰማራት ህብረተሰቡን እየጠበቁ እንደሚገኙም ተነግሯል።

የፌደራል መንግስት እና የክልሉ የፀጥታ ሀይሎች በመተከል ዞን በታጣቂዎች ላይ እርምጃዎችን እየወሰዱ እንደሚገኝ የገለፁት ሃላፊው በዚህም በርካቶች ተደምስሰዋል ነው ያሉት።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.