Fana: At a Speed of Life!

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች ለመፍታት ክልሉ ይሰራል- አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ከሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጋር በትብብር እንደሚሰራ አስታወቀ።

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ከሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጋር በቅርበት በመስራ ፓርኩ የሚገጥሙትን የተለያዩ ተግዳሮቶች በጋራ ለመፍታት እደሚሰሩ አስታወቁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ከክልሉ ከተወጣጡ ከ300 በላይ አመራሮች እና የተለያዩ ባለሙያዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አሰኪያጅ አቶ ፍጹም ከተማ ተገኝተዋል፡፡

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በግዝፈቱ ከአፍሪካ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዝ ሲሆን የተለያዩ አለምአቀፍ ስምና ዝናን ያተረፉ የአልባሳት አምራቾች እና ገዢዎች የሚገኙበት ፓርክ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታውቋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.